Slideshow image

ሚስዮናውያንን እናስብ!

በታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ክርስቲያን ሚስዮናውያን ነበሩ። እነዚህ ያለምንም ጥርጥር በክርስቶስ መንግስት ትልቅ ብድራት የሚጠብቃቸው ፤ ሁለንተናቸውን ለክርስቶስ ወንጌል የሰጡ ቅዱሳን ሰዎች ነበሩ። ብዙ ሚስዮናውያን በአለም ዙሪያ ታሪክ ያልተጻፈላቸው እንዳሉ እናውቃለን። በዘመናችንም አስደናቂውን የእግዚአብሔርን ምህረት ሰው በማይመርጠው ስፍራ የሚያገለግሉ ሚስዮናውያን አሉ።  ይህ ዋጋን ከፍሎ፤ቀዬንና ወገንን አልፎ በሌላ ህዝብ መካከል ማገልገል መንፈስ እንደገና እንዲያንሰራራልን ልንጸልይ ይገባናል። አጥቢያ ዘለል ብቻ ሳይሆን ብሄር ዘለል አገልጋዮች እንድሆን ለማበረታታት የቀድሞ ሚስዮናውያን ታሪክ  መካከል እስቲ 10ሩን ልጥቀስላችሁ፦ 

 

ዊሊያም ኬሪ / William Carey (1761-1834)

  • ዊሊያም ኬሪ/William Carey ትውልዱ እንግሊዛዊ የሆነ የዘመናዊው ሚሽን አገልግሎት አባት በመባል የሚታወቅ ነው። ያገለገለበት ስፍራ በህንድ ነበር።ኬሪ የቋንቋ ምሁርና ደራሲና አታሚ ነበር።  የመጽሐፍ ቅዱስ ከፊል በብዙ ቋንቋዎች ተርጉሟል። ኬሪ በእግንሊዝ ቤ/ክ ያደገ የጫማ ሰፊ ረዳት ሆኖ ሲሰራ የዳነ ሰው ነው። የመጥምቃውያን ቤ/ክ አባል ከሆነ በኋላ ሚስዮናዊ ሆኖ ወደ ህንድ ሄደ። ራሱን በራሱ ላቲን፥እብራይስጥና ግሪክኛ ተማረ። የመጥምቃውያን የሚስዮን ማህበር ሆኖ ብዙዎች ሚስዮናዊ እንዲሆኑ ተጽእኖ የፈጠረ ነው።  

አዶኒራም ጀድሰን/Adoniram Judson (1788-1850)

  • ጀድሰን ወደ ሜይማር በርማ ከሰሜን አሜሪካ የሄደ የመጀመሪያው ሚስዮናዊ ነበር። ከርሱ እንደቀደሙት ሚስዮናውያን ቤተክርስቲያን በመትከልና መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጎም ስራ ላይ ይተጋ ነበር። በህንድ በምእራብያውን ሚስዮናውያን ላይ ጥላቻ ሲበዛ ወደ በርማ ሄዶ በዚያ ያገለግል ነበር። የመጀመሪያዎቹን 18 አዲስ አማⶉች ለማግኘት 12 አመት ፈጅቶበታል። በሚሞትበት ጊዜ 100 አብያተ ክርስቲያናትና ከ8000 አባላት በላይ አፍርቶ ነበር። አሁን ላይ በሜይማር (በርማ) ያሉ የመጥምቃውያን አብያተ ክርስቲያናት “የጀድሰን ቀን•••Judson Day” በማለት አዶኒራም ጀድሰን በበርማ ያሉ ክርስቲያኖች ያከብራሉ። 

ዳዊት ሊቪንግስተን/David Livingstone (1813-1873)

  • ትውልዱ ስኮትላንዳዊ የሆነው ዳዊት ሊቪንግስቶስን ከለንደን የሚስዮናዊ ህብረት በህክምና ሚስዮናዊነት ወደ አፍሪካ የመጣ ሚስዮናዊ ነበር። በአፍሪካ ቆይታው ባብዛኛው ጊዜውን ያሳለፈው አህጉሪቱን በማጥናት explorer እና በህክምና ሞያ ነበር።ዳዊት ሊቪንግስተን በአፍሪካ በአንድ ስፍራ አልቆየም፤ከርሱ በኋላ ሌሎች ሚስዮናውያን ሲመጡ እንዲመቻቸው የአፍሪካን አህጉር አቀፍ ካርታ ይነድፍ ነበር። አገልግሎቱ ለሌሎች በር ከፋችን ነበር። 

ጆርጅ ሙለር/George Müller (1805-1898)

  • ሙለር ድሃ አደገ ህጻናትን አሳዳጊ ድርጅትን የጀመረና የጸሎት ተዋጊ በመሆኑ ይታወቃል። በስብከቱ ሁሉ ስለሚስዮናውያን አስፈላጊነት አበክሮ ይናገር ነበር። 10 ሺህ ህጻናት የሚያሳድግ ሰው ነበር። በእግዚአብሔር ታምኖ ያለማንም ርዳታ ሚስዮናዊ መሆንን “faith missions” የጀመረ ሰው ነበር። በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን በመታመን ማንንም ምንም ርዳታ ሳይጠይቅ ያገለግል ነበር። በእግዚዚአብሔርም ርዳታ ተሳክቶለት ነበር። 

ሃድሰን ቴይለር/Hudson Taylor (1832-1905)

  •    ሃድሰን ቴይለር 50 አመታት በሚስዮናዊነት በቻይና አገልግሏል። እንደዘመኑ እንግሊዞች በባህሉ ኩሩ ሳይሆን ራሱን ዝቅ አድርጎ እንደ ቻይናዎቹ ይለብስ ነበር። በአገሩ ሰዎችበዚህ ምክንያት በጣም ይተችና ይነቀፍ ነበር። ሆኖም ግን በቻይናዎቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጎታል። ሃድሰን ቴይለር የተማረ ሃኪም፥ወንጌላዊና የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ ነበር። የትርጉም ስራውን የጀመረውን ህክምና ሊያደርግ ወደ እንግሊዝ በተመለሰ ጊዜ ነበር። ከርሱ በኋላም ብዙ ሚስዮናውያን የርሱን የህይወት ታሪክ እያነበቡ ለሚስዮናዊነት ተነስተዋል። 

 

 

ጆናታን ጎፎርዝ/Jonathan Goforth (1859-1936)

  • ከሚስቱ ጋር በ1888 ለአጭር ጊዜ አገልግሎት ቻይና ከሚስቱ ጋር ሄዶ፤ በዚያው በመላው ቻይና እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰበከ

ኤሚ ካርሚካኤል/Amy Carmichael (1867-1951)

  • 56 አመት በህንድ ሚስዮናዊ ሆና ወደ ትውልድ አገሯ ወደ አየርላንድ ሳትመለስ አገለገለች፤ 
  • ቀዳሚ ስራዋ በደቡብ ህንድ ወላጅ አልባ ህጻናትን ታሳድግም ነበር። 
  • በሃድሰን ቴይለር አገልግሎት ልቧ ተቀጣጥሎ ወደ ቻይና ለመሄድ ብትፈልግም ለ20 አመታት የአልጋ ቁራኛ ሆና ሞተች

ኔት ሴይንት/Nate Saint (1923-1956)

  • Missionary Aviation Fellowship (MAF) pilot,የሚስዮን አውሮፕላን አብራሪ ነበር
  • በኤኳዶር ዋኦዳኒ ብሄርን ሲያገለግል ተገደለ 
  • በእህቱና አብረውት በተገደሉት ሚስዮናውያን ሚስቶች ብሄሩ ወንጌል ተሰበከለት 

ጂም ኤሊዬት/Jim Elliot (1927-1956)

  • ጂም የተወለደው በምእራብ አሜሪካ Portland, Oregon በሚባል ስፍራ ነው።
  • በ1950 የቋንቋን ትምህርት ለመማር ወደ ኦክላሆማ ሄደ፤ በዚያም ጽሁፍ የሌላቸውን ቋንቋዎች አጠና፤ በEcuadorian ደን ውስጥ የሚኖሩት የQuichuas ብሄሮች ሚስዮናዊ የሆነ ሰው አግኝቶ ስለብሄሩ ብዙ ተረዳ። ስለዚያም ይጸልይ ጀመረ nd l
  • ሆኖም 1956፥January 8 በዋኦዶኒ የብሄር ጦረኞች ከጓደኞቹ ጋር በአጭር ተቀጨ ተገደለ 

ኤሪክ ሊደል/Eric Liddell (1902-1945)

  • 1980s film Chariots of Fire. 
  • ከሚስዮናዊ ወላጆች በቻይና ተወለደ
  • ኦሎምፒክ ተወዳዳሪ ነበር 
  • በቻይና ሚስዮናዊ ነበር